Text copied!
CopyCompare
መጽሐፍ ቅዱስ - ወደ ሮሜ ሰዎች - ወደ ሮሜ ሰዎች 10

ወደ ሮሜ ሰዎች 10:9-17

Help us?
Click on verse(s) to share them!
9ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
10ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።
11መጽሐፍ። በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና።
12በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤
13የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።
14እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?
15መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ?
16ነገር ግን ሁሉ ለምሥራቹ ቃል አልታዘዙም። ኢሳይያስ። ጌታ ሆይ፥ ምስክርነታችንን ማን አመነ? ብሎአልና።
17እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።

Read ወደ ሮሜ ሰዎች 10ወደ ሮሜ ሰዎች 10
Compare ወደ ሮሜ ሰዎች 10:9-17ወደ ሮሜ ሰዎች 10:9-17