Text copied!
CopyCompare
መጽሐፍ ቅዱስ - ወደ ሮሜ ሰዎች - ወደ ሮሜ ሰዎች 3

ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23-28

Help us?
Click on verse(s) to share them!
23ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤
24በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
25እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥
26ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው።
27ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፥ በእምነት ሕግ ነው እንጂ።
28ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና።

Read ወደ ሮሜ ሰዎች 3ወደ ሮሜ ሰዎች 3
Compare ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23-28ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23-28