Text copied!
Bibles in Amharic

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:10-14 in Amharic

Help us?

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:10-14 in መጽሐፍ ቅዱስ

10 ነገር ግን አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ ጊዜ አጣችሁ እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር።
11 ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና።
12 መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ።
13 ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።
14 ሆኖም በመከራዬ ከእኔ ጋር ስለ ተካፈላችሁ መልካም አደረጋችሁ።
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4 in መጽሐፍ ቅዱስ