Text copied!
Bibles in Amharic

የዮሐንስ ወንጌል 9:6-12 in Amharic

Help us?

የዮሐንስ ወንጌል 9:6-12 in መጽሐፍ ቅዱስ

6 ይህን ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና።
7 ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው፤ ትርጓሜው የተላከ ነው። ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ።
8 ጐረቤቶቹም ቀድሞም ሲለምን አይተውት የነበሩ። ይህ ተቀምጦ ይለምን የነበረ አይደለምን? አሉ።
9 ሌሎች። እርሱ ነው አሉ፤ ሌሎች። አይደለም እርሱን ይመስላል እንጂ አሉ፤ እርሱ። እኔ ነኝ አለ።
10 ታድያ። ዓይኖችህ እንዴት ተከፈቱ? አሉት።
11 እርሱ መልሶ። ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ አድርጎ አይኖቼን ቀባና። ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሄደህ ታጠብ አለኝ፤ ሄጄ ታጥቤም አየሁ አለ።
12 ያ ሰው ወዴት ነው? አሉት። አላውቅም አለ።
የዮሐንስ ወንጌል 9 in መጽሐፍ ቅዱስ