Text copied!
Bibles in Amharic

የዮሐንስ ወንጌል 7:43-49 in Amharic

Help us?

የዮሐንስ ወንጌል 7:43-49 in መጽሐፍ ቅዱስ

43 እንግዲህ ከእርሱ የተነሣ በሕዝቡ መካከል መለያየት ሆነ፤
44 ከእነርሱም አንዳንዶቹ ሊይዙት ወደዱ ነገር ግን እጁን ማንም አልጫነበትም።
45 ሎሌዎቹም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን መጡ፤ እነዚያም። ያላመጣችሁት ስለ ምን ነው? አሉአቸው።
46 ሎሌዎቹ። እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም ብለው መለሱ።
47 እንግዲህ ፈሪሳውያን። እናንተ ደግሞ ሳታችሁን?
48 ከአለቆች ወይስ ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለን?
49 ነገር ግን ሕግን የማያውቀው ይህ ሕዝብ ርጉም ነው ብለው መለሱላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 7 in መጽሐፍ ቅዱስ