Text copied!
Bibles in Amharic

የዮሐንስ ወንጌል 5:5-11 in Amharic

Help us?

የዮሐንስ ወንጌል 5:5-11 in መጽሐፍ ቅዱስ

5 በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤
6 ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ። ልትድን ትወዳለህን? አለው።
7 ድውዩም። ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።
8 ኢየሱስ። ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው።
9 ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።
10 ያም ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው። ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት።
11 እርሱ ግን። ያዳነኝ ያ ሰው። አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 5 in መጽሐፍ ቅዱስ