Text copied!
Bibles in Amharic

የዮሐንስ ወንጌል 4:26-34 in Amharic

Help us?

የዮሐንስ ወንጌል 4:26-34 in መጽሐፍ ቅዱስ

26 ኢየሱስ። የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት።
27 በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን። ምን ትፈልጊያለሽ? ወይም። ስለ ምን ትናገራታለህ? ያለ ማንም አልነበረም።
28 ሴቲቱም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደች ለሰዎችም።
29 ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን? አለች።
30 ከከተማ ወጥተው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
31 ይህም ሲሆን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ። መምህር ሆይ፥ ብላ ብለው ለመኑት።
32 እርሱ ግን። እናንተ የማታውቁት የምበላው መብል ለእኔ አለኝ አላቸው።
33 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ። የሚበላው አንዳች ሰው አምጥቶለት ይሆንን? ተባባሉ።
34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 4 in መጽሐፍ ቅዱስ