Text copied!
Bibles in Amharic

የሐዋርያት ሥራ 27:32-36 in Amharic

Help us?

የሐዋርያት ሥራ 27:32-36 in መጽሐፍ ቅዱስ

32 ያን ጊዜ ወታደሮቹ የታንኳይቱን ገመድ ቈርጠው ትወድቅ ዘንድ ተዉአት።
33 ቀንም ሲነጋ ጳውሎስ ምግብ ይበሉ ዘንድ ሁሉን ይለምን ነበር፥ እንዲህም አላቸው። እየጠበቃችሁ ምንም ሳትቀበሉ ጦማችሁን ከሰነበታችሁ ዛሬ አሥራ አራተኛ ቀናችሁ ነው።
34 ሰለዚህ ምግብ ትበሉ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ ይህ ለደኅንነታችሁ ይሆናልና፤ ከእናንተ ከአንዱ የራስ ጠጕር እንኳ አትጠፋምና።
35 ይህንም ብሎ እንጀራን ይዞ በሁሉ ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ ቈርሶም ይበላ ዘንድ ጀመረ።
36 ሁለም ተጽናንተው ራሳቸው ደግሞ ምግብ ተቀበሉ።
የሐዋርያት ሥራ 27 in መጽሐፍ ቅዱስ