Text copied!
Bibles in Amharic

የሉቃስ ወንጌል 18:37-43 in Amharic

Help us?

የሉቃስ ወንጌል 18:37-43 in መጽሐፍ ቅዱስ

37 እነርሱም። የናዝሬቱ ኢየሱስ ያልፋል ብለው አወሩለት።
38 እርሱም። የዳዊት ልጅ፥ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ጮኸ።
39 በስተ ፊት ይሄዱ የነበሩትም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን። የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ።
40 ኢየሱስም ቆሞ ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ። በቀረበም ጊዜ። ምን ላደርግልህ ትወዳለህ? ብሎ ጠየቀው።
41 እርሱም። ጌታ ሆይ፥ አይ ዘንድ ነው አለው።
42 ኢየሱስም። እይ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው።
43 በዚያን ጊዜም አየ፥ እግዚአብሔንም እያከበረ ተከተለው። ሕዝቡም ሁሉ አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
የሉቃስ ወንጌል 18 in መጽሐፍ ቅዱስ