Text copied!
Bibles in Amharic

የሉቃስ ወንጌል 17:1-5 in Amharic

Help us?

የሉቃስ ወንጌል 17:1-5 in መጽሐፍ ቅዱስ

1 ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ። መሰናክል ግድ ሳይመጣ አይቀርም፥ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት፤
2 ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይጠቅመው ነበር።
3 ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው።
4 በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህ በቀንም ሰባት ጊዜ። ተጸጸትሁ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ፥ ይቅር በለው።
5 ሐዋርያትም ጌታን። እምነት ጨምርልን አሉት።
የሉቃስ ወንጌል 17 in መጽሐፍ ቅዱስ