Text copied!
CopyCompare
መጽሐፍ ቅዱስ - የዮሐንስ ወንጌል - የዮሐንስ ወንጌል 5

የዮሐንስ ወንጌል 5:4-9

Help us?
Click on verse(s) to share them!
4አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።
5በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤
6ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ። ልትድን ትወዳለህን? አለው።
7ድውዩም። ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።
8ኢየሱስ። ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው።
9ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።

Read የዮሐንስ ወንጌል 5የዮሐንስ ወንጌል 5
Compare የዮሐንስ ወንጌል 5:4-9የዮሐንስ ወንጌል 5:4-9