Text copied!
CopyCompare
መጽሐፍ ቅዱስ - የሐዋርያት ሥራ - የሐዋርያት ሥራ 13

የሐዋርያት ሥራ 13:1-4

Help us?
Click on verse(s) to share them!
1በአንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ።
2እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ። በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ።
3በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው።
4እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄዱ።

Read የሐዋርያት ሥራ 13የሐዋርያት ሥራ 13
Compare የሐዋርያት ሥራ 13:1-4የሐዋርያት ሥራ 13:1-4